በራሪ ወረቀቱን ለእርስዎ ለመላክ እና ስንት ሰዎች ኢሜሎቻችንን ሲከፍቱ ለማየት የኢሜል አድራሻዎን ብቻ እንጠቀማለን ፡፡ ሙሉ የግላዊነት ፖሊሲ እዚህ ሊታይ ይችላል ። ሐሳብዎን በማንኛውም ጊዜ መለወጥ እና ምርጫዎችዎን ማዘመን ወይም ከደንበኝነት ምዝገባ መውጣት ይችላሉ ፡፡

የኢትዮጵያ ህጻናት ጥናትና ፖሊሲ ፎረም

Students at Kokebe School in Addis Ababa. Photo: Alexandra Humme/GPE

የህጻናት ጥናትና ፖሊሲ ፎረም (CRPF) ሴሚናር ከ2018 ዓ.ም. ጀምሮ የሚካሄደው በሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒሰቴር ነው፡፡ ሲአርፒኤፍ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው በዲፊድ ፈንድ በሚደረገው የጌጅ ፕሮግራም ነው፡፡ ጌጅ የረጅም ጊዜ ጥናት ሲሆን ኢትዮጵን ጨምሮ የ20000 ሴትና ወንድ ታዳጊዎችን ህይዎት ይከታተላል፡፡ 

የሲአርፒኤፍ ሴሚናር በሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒሰቴር የሚከናወነው በወሩ መጨረሻ ባለው ሀሙስ ዕለት ነው፡፡ ዋና አላማውም በተመራማሪዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎችና ባለድርሻ አካላት መካከል የውይይት መድረክ መፍጠርና የጥናቶችን ውጤት ማሰራጨት ነው፡፡ የሲአርፒኤፍ ሴሚናር ሀሳብ አመንጪዎች በኢትዮጵያ ልጆች ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች፣ ፖሊሲና ተግባሮች መካከል ግንኙነት ለመፍጠር በማሰብ ከተለያዬ ተቋማት ኢመደበኛ ዉክልና የነበራቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ተቋማቶችም የአፍሪካ ህጻናት ፖሊሲ ፎረም (ACPF)፣ ቻዴት (CHAD-ET)፣ የክርስቲያን ተራድኦና ልማት ማህበር ጥምረት (CCRDA)፣ ዘላቂ የህጻናት ማብቃት ፎረም (FSCE)፣ ስርዓተ-ጾታና ታዳጊነት፡ አለማቀፍ ማስረጃ (ጌጅ) (GAGE)፣ የኖርዌጅያን ቸርች ኤይድ ፣ ኦክ ፋውንዴሽን ፣ ፕላን ኢትዮጵያ፣ ሪትራክ (RETRAK) ፣ ሴቭ ዘ ችልድረን ፣ ዩኒስፍ (UNICEF)፣ ወርልድ ቪዥን እና ያንግ ላይቭስ ናቸው፡፡

የበለጠ ይፈልጉ

በሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒሰቴር የሲአርፒኤፍ ወርሃዊ ሴሚናር የቀረቡትን አዲሱን የህጻናት ፖሊሲ እና የተለያዩ የጥናት ውጤቶችን ያካተተውን የመጋቢት 2011 ዓ.ም. የሩብ አመት መፅሄታችንን ያንብቡ፡፡

ለበለጠ መረጃ ኪሮስ ብርሀኑን ያግኙ፡፡