አካላዊ ነፃነት፣ ምሉዕነትና ከጥቃት ነጻ መሆን፡-በሀገሪቱ ዉስጥ ባለ የስርዓተ ፆታ ልማድ አማካኝነትሴትና ወንድ ታዳጊዎች ለተለያዩአይነት ጥቃቶች የተጋለጡ ናቸው፡፡ ሴት ታዳጊዎች ለህፃናት ጋብቻ፣ ለግርዛትና ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ ናቸው፡፡ ከአምስቱ ሴት ታዳጊዎች ሁለቱ ከ18 አመት በታች ያገባሉ፤ ግማሸ የሚሆኑት ይገረዛሉ፤ አንድሶስተኛ የሚሆኑት ከ15 –19 እድሜ ክልል ውስጥያሉ ያገቡ ሴቶች ደግሞ በትዳር አጋራቸው ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡ በሌላ ወንጀለኛ አካል የሚፈፀሙ ጥቃቶችም የተለመዱ ናቸው፡፡ በአንድ ጥናት እንደተመለከተው ከአስሩ ሴት ታዳጊዎች ዉስጥ ዘጠኙ አካላዊ ጥቃት ሲደርስባቸው ከአስሩ ዉስጥ ሰባቱ ደግሞ የስነ ልቦና ጥቃት ይደርስባቸዋል፤ ይህ የሚሆነው ብዙ ጊዜ በእናቶቻቸው እጅ ላይ ነው፡፡ወንድ ታዳጊዎች በቤት ውስጥም ሆነ በትምህርት ቤት አስቸጋሪባህሪ ይታይባቸዋል፡፡ብዙ ጊዜ በድብድብና በቡድን ጥቃትተሳታፊዎች ይሆናሉ፤ ለጥቃትም የተጋለጡ ናቸው፡፡
ጤና ፣ ስነ-ምግብና ስነ-ተዋልዶ ጤና፡-የጤና ኤክስቴንሽን ስራ በመስፋፋቱና የምግብ አቅርቦት በመሻሻሉየተነሳታዳጊዎች ለመሰረታዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ሆነዋል፤ ምግብም ከትልልቆች በተሻለ መልኩ ያገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ታዳጊዎች ስለፆታና ስነ-ተዋልዶጤና ያላቸው መረጃ የተለያዩ ናቸው፡፡ ስለወሊድ መቆጣጠሪያና ኤችአይቪ/ኤድስ ያላቸው መረጃ በጣም ሰፊ ነው፡፡ 61% የሚሆኑት ከ15 –19 አመት እድሜ ያላቸው ሴት ታዳጊዎች (እና 74% የሚሆኑት ወንድ ታዳጊዎች) ኤችአይቪ/ኤድስን በኮንዶም መከላከል እንደሚቻል እንደሚያዉቁና ልጃገረዶች ስለወሊድ መቆጣጠሪያ በራዲዮ (24%) ወይም በማህበረሰቡ በዓላት (27%) ላይ መረጃ ማግኘትእንደሚችሉ የ2016 ዲ.ኤች.ኤስ (DHS) ያመለክታል፡፡ ይሁን እንጅ በፆታና ስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ የሚሰጠው ትምህርትእጅግበጣም ጥቂት ነው፡፡ የማህበረሰቡ ልማድ በፆታ ዙሪያ የሚሰጡ ትምህርቶችን የተከለከለያደረገና የሴቶችን ፆታዊነት ያገለለ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ትናንሽ ታዳጊዎች ለጉርምስና ትምህርት ያላቸው መረጃ አነስተኛ ነው፤ የወር አበባን የሚጠብቁት በፍርሀትና በጭንቀት ነው፡፡በማህበረሰባዊገደብ አማካይነት ብዙ ልጃገረዶች ለወሊድ መቆጣጠሪያ ተደራሽ አይደሉም፡፡
የማህበራዊ ስነ-ልቦና ደህንነት፡-የታዳጊዎች ማህበራዊ ስነ-ልቦና ደህንነት የሚናውቀው በጣም ትንሽ ነው፡፡ ይሁን እንጅ የአእምሮ ጤና ችግር የብዙ ህፃናትና ታዳጊዎች (ከ12% እስከ25%) ህይወት ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ ያገቡና የቤት ዉስጥ ስራ የሚሰሩ ሴት ታዳጊዎች ከማህበረሰቡ የተገለሉ በመሆናቸው ለድብታና ጭንቀት የተጋለጡ ሆነዋል፡፡
የታዳጊዎችድምፅና ዉሳኔ ሰጭነት፡-የሴቶች ድምፅና ዉሳኔ ሰጭነት ተሳትፎ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ይህም የሆነው የማህበረሰቡ ልማድ ሴቶችን በዋናነት ዋጋ የሚሰጣቸውለሚስትነትና ለእናትነት ስለሆነነው፡፡ በተለይ ያገቡ ሴት ታዳጊዎች ከባሎቻቸው በእድሜ ያነሱ በመሆኑ የተነሳ ድምፅና ዉሳኔ ሰጭነታቸው በጣም ውስን ነው፡፡ ይሁን እንጂሴት ተዳጊዎች ለትምህርት እና ለትምሀርት ቤት ክበባትተደራሽ እየሆኑና የስራ እድልም እየተሻሻለ ሲመጣበህይወታቸው ንቁ ተሳታፊ መሆን ጀምረዋል፡፡
የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፡-በታዳጊዎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ዙሪያ የሚታወቀው ትንሽ ነው፡፡ትናንሽ ታዳጊዎች ከእይታ ውጭ ሲሆኑ ትልልቅ ታዳጊዎች ደግሞ የሚካተቱት “ወጣት” በሚባለው ሰፊ አውድ ውስጥነው፡፡ “ወጣት” የሚለው ቃል እስከ 30 እድሜ ያሉተን ወጣት ጎልማሶችንሁሉ ያካትታል፡፡ የስራ-አጥነት ምጥነት በወጣቶችና ሴቶች ዘንድ ከፍተኛነው፡፡ ይህም የሆነው ምንም እንኳ በሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት እድገት ቢኖርም እድገቱከህዝብ ቁጥር እድገትጋር ያልተመጣጠነነወ፡፡በዚህም የተነሳወጣቶችና ሴቶች በዝቅተኛ ክፍያ ስራናመደበኛ ባልሆኑ አነስተኛ የገበያ ስራዎች ላይ ጥገኛይገኛሉ፡፡
መረጃዎች፡-በኢትዮጵያ ታዳጊዎች ዙሪያ ብዙ ጥናታዊ መረጃዎች ይገኛሉ፤ በተለይም በትምህርት፣ በህፃናት ጋብቻና በስርዓተ-ፆታና ስነ-ተዋልዶ ጤና ዙሪያብዙ መረጃዎች አሉ፡፡ ይሁን እንጂሰፊ የሆነ የእድሜናየቦታ ልዩነት በቂ ትኩረት አለማግኘቱን የእኛ የመረጃ ካርታ በግልፅ ያሳያል፡፡ በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ ያለው ሰፊ የባህል ልማድና ድርጊቶችየታዳጊዎችን ህይወት እንዴት እየቀረፀ እንደሆነ ለመረዳት በቂ መረጃ የለም፡፡