ፍልስጤም
ፍልስጤም
ሀገራዊ ሁኔታ፡ በጋዛና ዌስት ባንክ የሚገኙ ታዳጊዎች የመጡት በረጅም ጊዜ ግጭት ና የእስራኤል ወረራ ውስጥ አልፈው ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት እንዳስጠነቀቀው ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የጋዛ ታዳጊዎች ሆነ ተብሎ እንዳያድጉ እየተደረገና አካባቢው በ2020 ሰው የማይኖርበት እንዲሆን እየተደረገ ነው፡፡ የዌስት ባንክ ህዝብም በእነርሱና በእስራኤል መካከል ስላለውና የሰዎችን እንቅስቃሴ ስላገደው የድንበር ችግር መፍታት አለባቸው፡፡ ለታዳጊዎች የሚቀርበው መሰረተ ልማት ከፍተኛ ቢሆንም፤ በግጭቱ ምክንያት የሚደርስባቸው የማህበራዊ ስነልቦና ጭንቀትና ለውሳኔ ሰጭነት ያላቸው እድል በጣም ፈታኝ ነው፡፡
ትምህርትና መማር፡ በጋዛና ዌስት ባንክ የሚገኙ ሴት ታዳጊዎች ከወንዶች በተሻለ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ይከታተላሉ፡፡ 80% የሚሆኑት የጋዛ ሴቶች ትምህርት ገበታ ላይ ሲገኙ የወንዶች ቁጥር ግን ከ67% ያነሰ ነው፡፡ በአለም ከፍተኛው የሰራ አጥነት የሚታዬው በጋዛ ቢሆንም ወንድ ታዳጊዎች ግን ቤተሰቦቻቸውን በኢኮኖሚ ለመደጎም ሲሉ ኢመደበኛ ስራ ይሰራሉ፡፡
የፆታና ስነ ተዋልዶ ጤና፡ ከ20 – 24 እድሜ ካላቸው ሴቶች ውስጥ ከአንድ አራተኛ በላይ የሚሆኑት ከ18 አመታቸው አስቀድሞ ልጅ ይወልዳሉ፡፡ በተጨማሪም የመውለድ ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ የወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀማቸው በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡
ስነ ምግብ፡ በምዕራባዉያን ዘንድ የተለመዱ ካሎሪ የሌላቸው ምግቦች በጋዛና በዌስት ባንክም እተለመዱ ሲሆን የአኗኗር ዘይቤያቸውም ከተመኛና መቀመጥ የበዛበት በመሆኑ ሴቶችም ሆነ ወንድ ታዳጊዎች ለአለቅጥ ዉፍርት እየተጋለጡ ነው፡፡ ስለማይንቀሳቀሱና ስፖርት ስለማይሰሩ በተለይ ሴቶች ተጎጅዎች ናቸው፡፡ ሲጋራ ማጨስ በወንዶች ዘንድ የተለመደ ነው፡፡
የማህበራዊ ስነልቦና ደህንነት፡ የጋዛን ኢኮኖሚ የጎዳውና ዌስት ባንክን በግንብና በሰፈራ ያጠረው የእስራኤል የማያቋርጥ የመሬት ወረራ ታዳጊዎችን ለከፍተኛ ድብርትና ጭንቀት አጋልጧቸዋል፡፡ ታዳጊዎች በግጭት ዉስጥ ይኖራሉ ፤ አካባቢያቸውም የወደፊት ህይወታቸውን ተስፋ ያጨለመ እንደሆነ በደደንብ ተገንዝበዋል፡፡ ግማሽ የሚሆኑት የጋዛ ታዳጊዎች ለእዕምሮን ሚያዛባ ገጠመኝ (PTSD) የተጋለጡ ናቸው፡፡ 80 የሚሆኑት የዌስት ባንክ ታዳጊዎች ደግሞ በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ የጥይት ተኩስ ድምፅ ይሰማሉ፡፡
ድምጽና ዉሳኔ ሰጭነት፡ የጆርዳንና የሌባኖን ታዳጊዎች ዕድሉን ባያገኙም የጋዛና የዌስት ባንክ ታዳጊዎች ግን የመሳተፍ እደሉ አላቸው፡፡ ይሁንና የፖለቲካል ተሳትፏቸው ግን በእስራኤል ወረራ አማካይነት ሊሳካ አልቻለም፡፡
የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፡ ትምህርት ቤት በመሆናቸውና የቤት ውስጥ ስራ ስለሚበዛባቸው አብዛኛው የጋዛና የዌስት ባንክ ሴት ታዳጊዎችና ወጣቶች ስራ ላይ ባይሆኑም፤ ስራ ከሚፈልጉት ውስጥ 80% የሚሆኑት ስራ ማግኘት አልቻሉም፡፡