ጥናት
ጥናት
A student studies in grade 8 at Shree Dharmasthali Lower Secondary School, Pokhara, Nepal. Photo: Jim Holmes/AusAID
ጌጅ የጥናት ፕሮግራም ለዘጠኝ አመት (ከ 2008 – 2017 ዓ. ም.) የሚካሄድ ድብልቅ የረጅም ጊዜ የምርምርና ግምገማዊ ጥናት ሲሆን የጥናት ፕሮግራሙ በተለያዬ ሁኔታ ላይ ባሉ ታዳጊ ሀገሮች ዉስጥ የሚኖሩ የታዳጊዎችን ህይወት ይከታተላል፡፡ ጌጅ የታዳጊዎች ህይወት መሸጋገር በሚችልበት ጉዳይ ላይ ማስረጃ መፈለግ ዋናው ግቡ ሲሆን ይህም ታዳጊዎችን ከድህነት ያላቅቃል፤ ለወጣቶች ለቤተሰቦቻቸውና ለማህበረሰቡም ፈጣን ማህበራዊ ለውጥ ያመጣል፡፡ ጌጅ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው ከእንግሊዝ መንግስት ከዩኬ ኤይድ (UK Aid) ነው፡፡
የእኛን ፅንሰ-ሀሳባዊ ማዕቀፍ ፣ የምርምር ዘዴ እና የምርምር ጥያቄዎችን በዝርዝር በመግለጽ በዚህ የ GAGE አጠቃላይ እይታ የበለጠ ይፈልጉ ፡፡