የጥናት ዘዴያችን
የጥናት ዘዴያችን
Adolescent girls study in Nepal. Photo: Jim Holmes/AusAID
ጌጅ መጠናዊና አይነታዊ የጥናት ዘዴዎችን በመቀላቅል ወደ ሁለተኛው አስርትና ጀማሪ ጎልማሳ የእድሜ ክልል የሚጓዙ ታዳጊዎችን የስርዓተ ጾታዊ ልምዶችና ተግባሮች ላይ ፍተሻ ያደርጋል፡፡
በተጨማሪም ታዳጊዎች ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞች ምን ያክል ሴትና ወንድ ታዳጊዎችን በመርዳትና ሙሉ አቅማቸው ላይ እንዲደርሱ በማገዝ ረገድ ስኬታማ እንደሆኑ ግምገማ እናደርጋለን፡፡
የኛ ጥናት ተጋላጭ ታዳጊዎች ላይ ልዩ አትኩሮት ያደርጋል፡፡ ይህም የአለማቀፉ የዘላቂ ልማት ዕቀድ (Sustainable Development Goals) “ማንም ወደ ኋላ እንዳይቀር” (Leave No One Behind) ከሚለው ተግባር ጋር አብሮ የሚሄድ ነው፡፡ የናሙና ተሳታፊዎቻችንም ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑትን፣ ስደተኞችን፣ የአካል ጉዳተኖችን፣ ያገቡና የተፋቱትን እንዲሁም የወለዱትን ያካትታል፡፡
በወረዳዎች፣ ክልሎች፣ ሀገሮችና አለምአቀፍ ደረጃ ያሉ ፍላጎቶችን መሰረት በማድረግና ልዩ ትኩረት በመስጠት ለታዳጊዎች ምቹ ሲስተም ፣ አገልግሎትና ፕሮግራም ከመፍጠር አኳያ የጥናቱ ዉጤት የፖሊሲና ፕሮግራም አውጭዎች ለታዳጊዎች የበለጠ መድረስ እንዲችሉ ይረዳል፡፡
ጌጅ ማለት፡
ጌጅ ተጋላጭ የሆኑ ታዳጊዎች በጥናቱ አማካይነት ምንም አይነት ጉዳት ዕንዳደርስባቸውና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ሁሉንም አይነት የስነምግባር መርሆዎች ይተገብራል፡፡
የኛ የስነምግባር መርህ የዲፊድን (DFID) የጥናትና ግምገማ ስነምግባር መርሆዎች ፤ የኢኮኖሚክ ኤንድ ሶሻል ሪሰርች ካዉንስል (2015) ስነምግባር መርሆዎች፤ የኦኢሲዲ (OECD) (2011) ሀገራት መርሆዎችን እና የሴቶችና ህጻናት ጥቃትን ለመቆጣጠር የአለም ጤና ድርጅትና የበሸታ መቆጣጠር ማዕከል ያወጣውን መመሪያ መሰረት ያደረገ ነው፡፡
የጌጅ ዋናው የጥናት መርህ የግለሰብም ሆነ የቡድን ጥናት ተሳታፊዎቻችንን ከማናኛውም አይነት ጉዳት ነጻ ማድርጋና ሰብዓዊ መብታቸውን መጠበቅ ነው፡፡ ለጥናታችንም ሆነ ለግምገማ የሚቀርቡ ተሳታፊዎች የሚመረጡት በፍላጎታውና በሙሉ ፍቃደኝነታቸው ብቻ ይሆናል፡፡ ተሳታፊዎች የሚሰጡት መረጃም ፍጹም ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ ይጠበቃል፡፡ እነዚህን መርሆዎች ወደ ተግባር የሚቀየሩት የአለማቀፍ የህጻናት መብት ድንጋጌዎችን (የህጻናት መብት ኮንቬንሽንና የህጻናት የመደመጥ መብት) መሰርት በማድረግ ሲሆን የሀገራትን ነባራዊ ሁኔታ ልዩነትም ግምት ውስት በማስገባትና በማክበር ነው፡፡
ለመስክ ስራ፣ የኦዲአይ (ODI) ጥናት ስነምግባር ኮሚቴ የእንግሊዝ ኢንስቲቱሽናል ሪቪው ቦርድ [IRB] ኦፍ ሪከርድ ሲሆን የጆርጅ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የአሜሪካ ኢንስቲቱሽናል ሪቪው ቦርድ [IRB] ኦፍ ሪከርድ ነው፡፡ በምንሰራባቸው ሀገሮች ሁሉ የሀገራቱን የስነምግባር መርሆዎች የምንከተልና ለተፈጻሚነቱም በየሀጋራቱ ካሉ ተመራማሪዎች ጋር በመመካከር እንሰራለን፡፡ ለሁሉም አለማቀፋዊና ሀገራዊ የጥናት አጋሮቻችን ለመነሻ (baseline) ጥናታችን የስነምግባር ማረጋገጫ አግኝተናል፡፡