በራሪ ወረቀቱን ለእርስዎ ለመላክ እና ስንት ሰዎች ኢሜሎቻችንን ሲከፍቱ ለማየት የኢሜል አድራሻዎን ብቻ እንጠቀማለን ፡፡ ሙሉ የግላዊነት ፖሊሲ እዚህ ሊታይ ይችላል ። ሐሳብዎን በማንኛውም ጊዜ መለወጥ እና ምርጫዎችዎን ማዘመን ወይም ከደንበኝነት ምዝገባ መውጣት ይችላሉ ፡፡

የፖሊሲ ትኩረት

Adolescents from Batu, Ethiopia © Nathalie Bertrams / GAGE 2021

የጌጅ ንድፈ ሀሳብና ጥናት የህጻናትን መብቶችና የፆታን እኩልነት በሚያቀነቅኑ አለማቀፋዊ ስምምነቶች የተሻሻለ ነው፡፡ እነዚህም የዘላቂ ልማት ዕቀዶች (SDGs) ፣ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን (UNCRC) እና ሴቶች ላይ የሚደርስ ማናቸውንም አይነት ማግለል ማስወገድ ኮንቬንሽን (CEDAW) ያካትታል፡፡ ጌጅ ታዳጊዎች ብቻ ላይ ሳይሆን አትኩሮት የሚያደርገው ተጋላጭ ታዳጊዎች ላይ በተለይም የአካል ጉዳተኞች፣ ስደተኞች፣ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች እና በልጅነት ያገቡ ልጃገረዶች ላይ ነው፡፡ ይህም ከላይ የተጠቀሱትን ስምምነቶች በተግባር ለማዋል ይረዳል፡፡ የጌጅ የጥናት ማስረጃ የታዳጊዎችን እድሜና ፆታ ተኮር ፍላጎት የሚገባዉን አትኩሮት እንዲያገኝና አላቀፋዊ ስምምነቶች እንዴት ወደተግባር መቀየር እንዳለባቸው ለመረዳት ያግዛል፡፡ የረጅም ጊዝ ጥናታችን የፖሊሲ አውጭዎችና የፕሮግራም ተግባሪዎች ስራዎቻቸውን በሚገባ እንዲተገብሩና ለተጋላጭ ታዳጊዎች አስፈላጊዉን ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ ያግዛል፡፡ ለጌጅ ጥናት አስፈላጊ ከሆኑት አላቀፋዊ ስምምነቶች ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉትናቸው፡፡

የዘላቂ ልማት ዕቀዶች

በአሁኑ ወቅት የታዳጊዎች ብዛት 1.2 ቢሊዬን ቢደርስም፤ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የወጣቶችን ቁጥር በአለማችን ቢታይም፤ በፖሊሲ ዎችና ፕሮግራሞች ግን በሚገባ አልተወከሉም፡፡ የታዳጊዎችን ህይወት ማጥናት ከልጅነት ወደ ጎልማሳነት የሚሸጋገሩበትን መንገድ በተገቢው መልኩ መተለም ብቻ ሳይሆን የ2030 የዘላቂ ልማት ዕቀዶችንም ማሳካት ነው፡፡ ምንም እንኳ 17 የዘላቂ ልማት ዕቀዶችና 169 ኢላማዎች (targets) ከ230 ተናጠላዊ ጠቋሚዎች (indicators) ጋር የተቀናጁ ቢሆንም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ጠቋሚዎች ወደተግባር ለመቀየር የሚያስችል ማስረጃ የላቸውም፡፡ አንደኛውና ዋነኛው የጌጅ አላማ የሴትና ወንድ ታዳጊዎችን ህይዎት ለመከታተል የሚያስችል የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችንና ዘዴዎችን ማዘጋጀት ነው፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘረው የዘላቂ ልማት ዕቅዶችና ኢላማዎች እንዴት የታዳጊዎችን ደህንነት ማሻሻል እንደሚችሉ የነደፍንበት ነው፡፡

1. አልቦ ድህነት    
 • • የየሀገሩን ፍች መሰርት በማድረግ በድህነት የሚኖሩትን ልጆች ቁጥር ቢያንስ በግማሽ መቀነስ (ኢላማ 1.2)፡፡

2. ዜሮ ርሃብ

 • • መንኛውንም አይነት የስነምግብ እጥረት ማስወገድና የሴት ታዳጊዎችን የምግብ ፍላጎት ማሟላት (ኢላማ 2.2)፡፡

3. ጥሩ ጤናና ደህንነት

 • • የአለምን የእናቶች ሞት መጠን መቀነስ (ኢላማ 3.1)፡፡
 • • የቤተሰብ ምጣኔ ፣ መረጃና ትምህርት ፣ እንዲሁም ስነ ተዋልዶን ከብሄራዊ ስትራቴጅና ፕሮግራም ጋር ያጣመረ አለማቀፋዊ የፆታና ስነ ተዋልዶ ጤና ክብካቤ አገልግሎትን ማረጋገጥ (ኢላማ 3.7)፡፡
 • • የአእምሮ ጤናና ደህንነትን ማሻሻል (ኢላማ 3.4)፡፡

4. ጥራት ያለው ትምህርት

 • • ሁሉም ሴትና ወንድ ታዳጊዎች ስኬታማ ሊደርጋቸው የሚችል ነፃና ጥራት ያለው የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምሀርት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ (ኢላማ 4.1)፡፡
 • • በ2030 ፤ ለሁሉም ሴቶችና ወንዶች ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያና የዩኒቨርስቲ ትምህርት እኩል ተደራሽነትን ማረጋገጥ (ኢላማ 4.3)፡፡
 • • ልጆችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ስርዓተ ጾታን ማዕከል ያደረጉና ለሁሉም ተስማሚ፣ የማይረብሽ፣ አቃፊና ስኬታማ የትምህርት ከባቢ የሚፈጥሩ የትምህርት ግብዓቶችንና ቁሳቁሶችን መገንባትና ማሻሻል (ኢላማ 4.a)፡፡

5. የስርዓተ ፆታ እኩልነት

 • • በየትኛውም ቦታና በሁሉም ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚደርስን ማንኛውንም አይነት ማግለልን ማስወገድ (ኢላማ 5.1)፡፡
 • • ስደትም ይሁን ጾታዊ በሁሉም ልጃገረዶች ላይ በማህበረሰብና በግል ረረጃ የሚደርስን ማንኛውንም አይነት ጥቃት ማስወገድ (ኢላማ 5.2)፡፡
 • • የህጻናት፣ ያለዕድሜና አስገዳጅ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛት የመሳሰሉ ማንኛውንም አይነት ጎጅ ልማዳዊ ድርጊት ማስወገድ (ኢላማ 5.3)፡፡
 • • ያለ ክፍያ የሚሰሩትንና የቤት ዉስጥ ስራን እዉቅናና ዋጋ መስጠት (ኢላማ 5.4)፡፡
 • • የጾታ እኩልነትንና የሴቶችን በሁሉም ደረጃ ተጠቃሚነት ለማስሻሻል የሚያስችሉ ጥሩ ጥሩ ፖሊሲዎችና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ህጎችን መቅረፅና ማጠናከር (ኢላማ 5.c)፡፡

6. ንፁህ ውሀና ንፅህና

 • • በ2030፤ሴቶች፣ ልጃገረዶችና ተጋላጭ የሆኑት ላይ ልዩ አትኩሮት በማድረግ ለሁሉም በቂና ተደራሽ የሆነ ንፅህናና ፅዳት ማሳካት (ኢላማ 6.2)፡፡

8. ጥሩ ስራና ምጣኔ ሀብታዊ እድገት

 • • ለሁሉም ወጣቶች ሙሉና ስኬታማ ቅጥርና ጥሩ ስራን ማሳካት፤ ለተመሳሳይ ስራ ተመሳሳይ ክፍያን ማሳካት (ኢላማ 8.5)፡፡
 • • በ2020፤ ከቅጥር፣ ትምህርትና ስልጠና ውጭ የሆኑ ወጣቶችን ቁጥር በጉልህ መቀነስ (ኢላማ 8.6)፡፡
 • • ህገ ወጥ የግዳጅ ስራን ፣ ዘመናዊ ባርነትንና የሰዎች ዝውውርን ለማስወገድ ፈጣንና ስኬታማ እርምጃ መውሰድ፤ ቅጥርንና ወታደርነትን ጨምሮ በ2025 አስከፊውን የህጻናት ስራ በማንኛውም መልኩ ማስወገድ (ኢላማ 8.7)፡፡
 • • የሰራተኞችን መብት ማስጠበቅና ስደተኛና ሴት ሰራተኞችን ጨምሮ ለሁሉም ሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ ከባቢ መፍጠር (ኢላማ 8.8)፡፡
 • • በ2020፤ በወጣቶችን ቅጥር ዙሪያ ያለውን አለማቀፋዊ ስትራቴጂ መተግበርና ማሳደግ፤ የአለማቀፍ ሰራተኛ ማህበርን አለማቀፍ ስራ ማዕቀፍ (Global Jobs Pact) መተግበር (ኢላማ 8.b)

11. ዘላቂ ከተሞችና ማህበረሰቦች  

 • • ደህንነቱ የተጠበቀ፣ መቹ፣ ተደራሽና ዘላቂ የትራነሰፖረት ሁኔታ መፍጠር፤ ለልጆች የተለዬ ትኩረት በመስጠት የህብረተሰብ ትራንስፖርትን ማስፋፋትና የመንገድ ደህንነት ማሳደግ (ኢላማ 11.2)፡፡
 • • ለልጆች የተለዬ ትኩረት በመስጠት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አቃፊና ተደራሽ የሆነ አረንጓዴና ምቹ የሆነ ቦታን መፍጠር (ኢላማ 11.7)፡፡

13. አየር ንብረት

 • • ለወጣቶች የተለዬ ትኩረት በመስጠት ታዳጊና ጥቃቅን ደሴት ሀገሮቸን ያማከለ የአየር ንብረት ለውጥን በስኬት ለመከላከል የሚያስችሉ መንገዶችን ማሳፋፋት (ኢላማ 13.b)፡፡

16. ሰላም ፣ ፍትህና ጠንካራ ተቋማት

 • • ሁሉንም አይነትና በሁሉም ቦታ ጥቃትና ተዛማጅ የሞት መጠንን በጉልህ መቀነስ (ኢላማ 16.1)፡፡
 • • የልጆችን ጉዳት፣ ብዝበዛ፣ የሰዎች ዝውውርና ተዛማጅ ጥቃቶችን ማስቆም (ኢላማ 16.2)፡፡
 • • በሀገርና አለምአቀፍ ደረጃ የህግ የበላይነትን ማስፈንና ፍትህን ለሁሉም ማዳረስ (ኢላማ 16.3)፡፡
 • • ሀላፊነት የተሞላበት፣ አቃፊ፣ አሳታፊና ወካይ ዉሳኔ ሰጭነትን በሁሉም ደረጃ ማረጋገጥ (ኢላማ 16.7)፡፡

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን (UNCRC) የልጆችን መብት ለመጠበቅና ከዚህ ጋር ያለውን የመንግስት ሀላፊነት የሚገለፅ አለማቀፋዊ ስምምነት ነው፡፡ ከአሜሪካ በስተቀር በ200 የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገሮች ተቀርጾና ተፈርሞ እኤአ ከ1990 ጀምሮ በተግባር ላይ ዉሏል፡፡ ይህ የህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን ታዳጊዎችን ለብቻቸው አይጠቅስም፤ ከ18 አመት በታች ያሉትን በሙሉ ልጅ ብሎ ሲገልጻቸው ጌጅ የሚያተኩርባቸውን ታዳጊዎችም ያጠቃልላል ፡፡ ይህ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮንቬንሽንና ሶስቱ “አማራጭ ፐሮቶኮሎች” የልጆችን የመኖርና የማደግ መብት እውቅና ይሰጣሉ፤ ከጉዳት የመጠበቅ፣ በፍላጎታቸው ከመረጡት ሰው ጋር የማደግና ድምፃቸው እንዲሰማ የማድረግ መብትን ያጎናጽፋል፡፡ መንግስታቶች በልጆች መብት ዙሪያ ያሉትን ሀገራዊ ለዉጦች በየአመቱ ለልጆች መብት ኮሚቴ ሪፖርት እንዲያደርጉ ይደነግጋል፡፡ ኮሚቴው ደግሞ በሚሻሻልበት ዙሪያ ለሀገራት ምክረ ሀሳብ ይሰጣል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን 54 አንቀፆችን የያዘ የልጆችንና የወላጆችን መብቶች የቀፈ ረጅምና ሰፊ ዶክመንት ነው፡፡ ሌሎችም ህፃናትን ለመረዳትና ልዩ የሆነውን ፍላጎታቸውን ለማወቅ የሚያስችሉ ርዕሶችን አካቷል፡፡

ሴቶች ላይ የሚደርስ ማናቸውንም አይነት ማግለል ማስወገድ ኮንቬንሽን

ሴቶች ላይ የሚደርስ ማናቸውንም አይነት ማግለል ማስወገድ ኮንቬንሽን (CEDAW) የሴቶችን መብት ለመጠበቅ የወጣ አለማቀፋዊ ስምምነት ነው፡፡ ይህ ኮንቬንሽን የተቀረጸው በየተባበሩት መንግስታት እኤአ በ1979 ሲሆን ታዳጊዎችን ለብቻቸው አይጠቅስም፡፡ ይሁን እንጅ የተዘጋጀበት ቋንቋ “ሴቶችና ልጃገረዶች” ስለሚል ኮንቬንሽኑ ጌጅ የሚያተኩርባቸውን ሴት ታዳጊዎች ያካትታል፡፡ ሴቶች ላይ የሚደርስ ማናቸውንም አይነት ማግለል ማስወገድ ኮንቬንሽን ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚከሰትን ማግለል ሲተነትን ማንኛውንም አይነት ጾታን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን እንዳይጠቀሙ ሊያደርግ የሚችል ማግለል በሚል ነው፡፡ ምንም እንኳ የጌጅ ተወካይ ሀገሮችን ጨምሮ ወደ 200 የሚሆኑ ሀገራት ቢፈርሙትም፤ ብዙዎች ይህን ያደረጉት በሙሉ ልብ አይደለም፡፡ ከጌጅ ተወካይ ሀገሮች ዉስጥ ሪዘርቬሽን ያላት ባንግላዲሽ ብቻ ነች ፤ ይህም በጋብቻ እኩልነት ዙሪያ ላይ ባለው አንቀጽ ላይ ነው፡፡ ኮንቬንሽኑን የፈረሙ ሀገራት በስርዓተ ፆታ እኩልነት ዙሪያ አፈጻጸማቸውን ለሴቶች ላይ የሚደርስ ማናቸውንም አይነት ማግለል ማስወገድ ኮንቬንሽን ኮሚቴ አመታዊ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይጠበቃል፡፡ ኮሚቴው ደግሞ በሚሻሻልበት ዙሪያ ለሀገራት ምክረ ሀሳብ ይሰጣል፡፡ ይህ ኮንቬንሽን የሴቶችንና ልጃገረዶችን መብቶች ያቀፉ 30 አንቀፆችን ይዟል፡፡ ሌሎች ትኩረት የሚፈልጉ አካላቶች ለምሳሌ የህፃናት ጋብቻ እና ግዳጅ ጋብቻ ፣ የሰዎች ዝውውር፣ ፆታዊ ጥቃት ያጋጠማቸውና በገጠር የሚኖሩ ታዳጊዎች ፍላጎትንም በተገቢው ሁኔታ አካቷል፡፡

የቤጂንግ የተግባር መግለጫና ሰነድ

የቤጂንግ የተግባር መግለጫና ሰነድ የተቀረፀው ቤጂንግ ላይ በተካሄደው አለም አቀፉ የሴቶች ኮንፈረስ እኤአ በ1995 ሲሆን የሴቶችንና ልጃገረዶችን ሰብዓዊ መብት ለመጠበቅ ታስቦ የወጣ አለማቀፋዊ ስምምነት ነው፡፡ ከሴቶች ላይ የሚደርስ ማናቸውንም አይነት ማግለል ማስወገድ ኮንቬንሽን የበለጠ ጥልቅ የሆነና ከየተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን የበለጠ ስርዓተ ፆታ ላይ ያተኮረ የልጃገረዶችን ልዩ ፍላጎት በደንብ የለዬ ስምምነት ነው፡፡ የቤጂንግ ሰነድ በ200 ሀገራት ዘንድ ድጋፍ ቢያገኝም ህጋዊ ማዕቀፍ ግን አላገኘም፡፡ ይሁን እንጅ ሀገራት ተከታታይ ሪፖረቶችን እነዲያቀርቡ ያደርጋል፡፡ በየአምስት አመቱ የሚካሄደው የአለማቀፍና ሀገራቀፍ አፈጻጸም ግምገማ በሚቀጥለው 2020 የሚካሄድ ሆናል፡፡ የቤጂንግ ሰነድ 12 ጉዳዮችን ያቀፈ ሲሆን አብዛኛው ስለ ታዳጊዎችና ሴት ልጆች ነው፡፡ በድህነትና በግጭት ውስጥ ከሚኖሩት እስከ በፖለቲካ ወሳኝ ቦታ ላይ ያሉ ሴቶች ሁኔታ ይዳስሳል፤ የሴቶችና የልጃገረዶች መብት በሚጎለብትበት ተቋማዊ ሁኔታም ያጠነጥናል፡፡ በተለይ የሚያተኩረው የመጨረሻው ክፍል ለጌጅ አስፈላጊ ነው፡፡ ሴት ልጆችን የሚመለከተው ክፍል ዉስጥ ያሉት ዘጠኙ ስትራቴጂክ አላማዎች ጌጅ ለታዳጊዎች ህይወት ወሳኝ ናቸው ብሎ ከቀረፃቸው አቅሞች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውና አሉታዊ የሆኑ ባህላዊና ተግባራዊ ልማዶችን ማስወገድ ላይ ጠንካራ አትኩሮት ያደርጋል፡፡