በራሪ ወረቀቱን ለእርስዎ ለመላክ እና ስንት ሰዎች ኢሜሎቻችንን ሲከፍቱ ለማየት የኢሜል አድራሻዎን ብቻ እንጠቀማለን ፡፡ ሙሉ የግላዊነት ፖሊሲ እዚህ ሊታይ ይችላል ። ሐሳብዎን በማንኛውም ጊዜ መለወጥ እና ምርጫዎችዎን ማዘመን ወይም ከደንበኝነት ምዝገባ መውጣት ይችላሉ ፡፡

ስለኛ

ስለኛ

Adolescent girls in Ethiopia. Photo: Nathalie Bertrams/GAGE

የስርዓተ ፆታና ታዳጊነት፡ አለማቀፋዊ ማስረጃ (ጌጅ) የጥናት ፕሮግራም ለዘጠኝ አመት (ከ 2008 – 2017 ዓ. ም.) የሚካሄድ ድብልቅ የረጅም ጊዜ ምርምርና ግምገማዊ ጥናት ነው፡፡ በአጠቃላይ የጥናት ፕሮግራሙ የ20000 ታዳጊዎችን ህይወት በስድስት ዝቀተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገሮች (ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በአፍሪካ ፣ ባንግላዲሽና ኔፓል በኤዥያ እና ጆርዳንና ሊባኖስ በመካከለኛው ምስራቅ) ላይ ይከታተላል ፡፡

ጌጅ የታዳጊዎች ህይወት መሸጋገር በሚችልበት ጉዳይ ላይ መረጃ መፈለግ ዋናው ግቡ ሲሆን ይህም ታዳጊዎችን ከድህነት ያላቅቃል፤ ለወጣቶች ለቤተሰቦቻቸውና ለማህበረሰቡም ፈጣን ማህበራዊ ለውጥ ያመጣል፡፡

የጌጅ የጥናት ጥምረት በኦቨርሲስ ዴቨሎፕመንት ኢንስቲቱት (ኦዲአይ) (Overseas Development Institute (ODI)) የሚመራ ሲሆን 35 የሚሆኑ ታላላቅና በስራው ሰፊ ልምድ ያላቸው አለማቀፋዊ የጥናትና ምርምር ፣ የፖሊሲና ፕሮግራም ተባባሪ ተቋማትን አሰባስቦ የያዘ ነው፡፡ ጌጅ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው ከእንግሊዝ መንግስት ከዩኬ ኤይድ ነው፡፡

የእኛን ፅንሰ-ሀሳባዊ ማዕቀፍ ፣ የምርምር ዘዴ እና የምርምር ጥያቄዎችን በዝርዝር በመግለጽ በዚህ የ GAGE አጠቃላይ እይታ የበለጠ ይፈልጉ ፡፡