በራሪ ወረቀቱን ለእርስዎ ለመላክ እና ስንት ሰዎች ኢሜሎቻችንን ሲከፍቱ ለማየት የኢሜል አድራሻዎን ብቻ እንጠቀማለን ፡፡ ሙሉ የግላዊነት ፖሊሲ እዚህ ሊታይ ይችላል ። ሐሳብዎን በማንኛውም ጊዜ መለወጥ እና ምርጫዎችዎን ማዘመን ወይም ከደንበኝነት ምዝገባ መውጣት ይችላሉ ፡፡

የጥናታችን ጥያቄዎች

Secondary school students on a break, Bangladesh. Photo: ADB

ከፅንሰሀሳብ ንድፉ ላይ በመነሳት ጌጅ የሚከተሉት ሶስት ዋና ዋና ጥያቄዎች ላይ ያተኩራል፡፡ እነዚህም፡

1. በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው የተለያዩ ሀገሮች ዉስጥ የሚኖሩ ታዳጊዎች ከልጅነት ወደ ጎልማሳነት እንዴት ይሸጋገራሉ?

 • • የታዳጊዎች ተሞክሮና ልምድ ከእድሜ ፣ ፆታ፣ አካል ጉዳትና አካባቢ ሁኔታ አንጻር እንዴት ይለያያል?
 • • የታዳጊዎች ህይወትና ተሞክሮ ከስርዓተ ፆታ አንጻር ምን ይመስላል?
 • • ታዳጊዎች የቀን ተቀን ህዎታቸው ላይ ተፅዕኖ ያለውን የስርዓተ ፆታ ልማድና አድሏዊ እሳቤን እንዴት ይመለከቱታል?
 • • ወላጆች ፣ ቤተሰቦች ፣ ማህበረሰብ ፣ አገልግሎት ሰጪዎችና ሚድያው በታዳጊዎች ህይወት ላይ የሚጫወተው ሚና ምንድን ነው?
 • • ታዳጊዎች እነሱን ስለሚጠቀሟቸው አገልግሎትና ተቋማት ምን ያስባሉ (ለምሳሌ - ትምህርት ቤቶች ፣ ጤና ጣቢያዎች ፣ ፍትህ ፣ ወዘተ፡፡)?
 • • ተቋማት፣ ፖሊሲዎችና ህጋዊ ንድፎች የታዳጊዎችን ህይዎትና እድገት እንዴት መለወጥ ይችላሉ?

2. ፕሮግራሞችና ፖሊሲዎች በታዳጊዎች ላይ ምን ተፅዕኖ አላቸው?

 • • በታዳጊዎች አቅሞች ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞች የሚኖራቸው የአጭርና ረጅም ጊዜ ተፅዕኖ ምንድን ነው?
 • • ፕሮግራሞች በቤተሰብ ፣ አቻ እና በማህበረሰብ አመለካከት ፣ ተግባርና ልማድ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ምንድን ነው?
 • • የታዳጊ ተኮር ፕሮግራሞች ከተዛማች አገልግሎቶችና ስርዓቶች ጋር (ለምሳሌ ትምህርት ፣ ጤና ክብካቤ ፣ ፍትህ፣ ወዘተ፡፡) እንዴት ይጣመራል?

3. በታዳጊዎች አቅሞች ላይ ትልቁን ተፅዕኖ ማድረግ የሚችሉ የትኞቹ የፕሮግራም ባህሪያት አይነቶች ናቸው?

 • • ለእያንዳነዷ አቅም ወይም ደረጃ የተቀረጹ ትግበራዎች ለሁሉም አቅሞች ከተዘጋቹ የዘርፈ ብዙ አይነት ፕሮግራሞች ጋር ሲነጻጸሩ ውጤታማ ናቸው?
 • • የተለያዩና ተዛማች ፕሮግራም ትግበራዎች ቅደም ተከተል ምን መምሰል አለበት?
 • • የትኞቹ ትግበራዎችና ክፍሎቻቸው የተለያዬ የእድሜ ክልል ላይ ያሉ ታዳጊዎች ላይ ተፅዕኖ አላቸው?
 • • የፕሮግራሞች ትግበራ በምን ያክል ጊዜና ለምን ያክል ጊዜ መካሄድ አለባቸው?
 • • የፕሮግራም ግብዓቶች (በጀት ፣ የሰው ሀይልና መሰረተ ልማት) ምን ያህል አፍላ ወጣቶችን ያማከሉ ናቸው?
 • • የፕሮግራሞች ቀረፃ ፕሮግራሞች እንዲያድጉና ለሌሎች ታዳጊዎች መድርስ እንዲችሉ ተጽዕኖ ማድረግ ይችላሉ?