በራሪ ወረቀቱን ለእርስዎ ለመላክ እና ስንት ሰዎች ኢሜሎቻችንን ሲከፍቱ ለማየት የኢሜል አድራሻዎን ብቻ እንጠቀማለን ፡፡ ሙሉ የግላዊነት ፖሊሲ እዚህ ሊታይ ይችላል ። ሐሳብዎን በማንኛውም ጊዜ መለወጥ እና ምርጫዎችዎን ማዘመን ወይም ከደንበኝነት ምዝገባ መውጣት ይችላሉ ፡፡

የኛ የጥናት ዘዴ

Adolescents with hearing impairments, Ethiopia. Photo: Nathalie Bertrams/GAGE

ጌጅ አዳዲስ የረጅም መጠናዊና አይነታዊ መረጃዎችን ለመሰብሰብና ለመተንተን የሚያስችለውን የድብልቅ የጥናት ዘዴን (mixed-methods research approach) ይከተላል፡፡ ይህ የድብልቅ የጥናት ዘዴ በሁለተኛው አስርት አመታት ላይ ያሉ የታዳጊዎችን ልምድ በደንብ ለመረዳት ያስችላል፡፡ የትኛው የለውጥ ስትራቴጂ ለየትኞቹ ታዳጊዎች፣ በየትኛው የእድሜ ክልልና በየትኛው ነባራዊ ሁኔታ የበለጠ ይሰራል የሚለውን ለመረዳት ይረዳል፡፡

 

ከ10 - 19 ባሉ ታዳጊዎች ላይ በሶስት ዙር መረጃን እንሰበስባለን፡፡ የኛ መጠናዊ ጥናት ከ2009 – 2011፣ ከ2011 – 2013 እና ከ2013 – 2015 የሚከናዎን ይሆናል፡፡ የመረጃ ስብሰባው በየሀገራቱ የሚከናወነው ለመማማር ነው፡፡ የኛ አይነታዊ ጥናት “ለታዳጊዎች የሚሰራው ምንድን ነው” የሚለውን ለመረዳት ያስችል ዘንድ የመጠናዊ ጥናቱን የመጀመሪያ ትንተና ተከትሎ የሚመጣ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፣ ምን ያህል ታዳጊዎች በትምህርት ገበታ ላይ ይገኛሉ፤ ምን ያህሉስ የጤና ስነ-ተዋልዶ አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው? ቃለ መጠይቁ “ለምን” የሚለዉን ለመረዳት ያስችላል፡፡ ለምሳሌ - ለምን ትምህርታቸውን አቋረጡ እና ለምን የጤና ስነ-ተዋልዶ አገልግሎት ተጠቃሚ አልሆኑም?