በራሪ ወረቀቱን ለእርስዎ ለመላክ እና ስንት ሰዎች ኢሜሎቻችንን ሲከፍቱ ለማየት የኢሜል አድራሻዎን ብቻ እንጠቀማለን ፡፡ ሙሉ የግላዊነት ፖሊሲ እዚህ ሊታይ ይችላል ። ሐሳብዎን በማንኛውም ጊዜ መለወጥ እና ምርጫዎችዎን ማዘመን ወይም ከደንበኝነት ምዝገባ መውጣት ይችላሉ ፡፡

የፅንሰ ሀሳብ ንድፍ

Students attend class at the Kamrun Nessa Government Girls School in Dhaka. Photo: Abir Abdullah/ADB

የጌጅ ፅንሰ ሀሳብ ንድፍ አሁንም ሆነ ወደፊት የአፍላ ወጣቶችን እድገትና አቅም በሚገባ ለመረዳትና ለማዳበር ስለሚያስችል የሁለንተናዊ (Holistic) ፅንሰሀሳብ ንድፍን ይከተላል፡፡ በተለይም ስርዓተ ፆታ ተኮር የሆኑ አድሏዊ ልምድና ተግባር ከሌሎች ማህበራዊ ጉዳቶችና መልካም አጋጣሚዎች ጋር ያለዉን ተዛምዶ ይዳስሳል፡፡ የኛ ፅንሰ ሀሳብ ንድፍ የሚያተኩረው፡

  • . የታዳጊዎች አቅሞች - የታዳጊዎች ደህንነት መሰረት የሆኑ ስድስት ግለሰባዊና ማህበራዊ አቅሞች ፡ ትምህርትና መማር ፣ አካላዊ ምሉዕነት (ከፆታዊና ስርዓተ ፆታ ጥቃትና ያለእድሜ ጋብቻ ነፃ መሆን) ፣ የአካላዊና መራባት ጤንነትና ስነ-ምግብ ፣ የማህበራዊ ስነ ልቦና ደህንነት ፣ ድምጽና ውሳኔ ሰጭነት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፡፡
  • . የለዉጥ መንገዶች - ሁለንተናዊ ለዉጥን ለማምጣት ተከታታይ የሆኑ ተግባሮችን በግለሰብ ፣ በቤተሰብ ፣ በማህበረሰብ ፣ በአገልግሎቶችና በተቋም ደረጃ ፍተሻ ማድርግ፡፡
  • . ነባራዊ ሁኔታዎች - የታዳጊዎች ህይወትና እድገት ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ አካባቢያዊ ፣ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ማጥናት፡