ባንግላዲሽ
ባንግላዲሽ
የኛ ጥናት፡ በደለላማዉ ምስራቅ ህንድ በኩል በምትገኘው ባንግላዲሽ 1900 ሴትና ወንድ ተዳጊዎችን በገጠራማዋ ቺታጎንግና በዳካ ከተማ እንከታተላለን፡፡ በተጨማሪም 1800 የሮሂንጋ ስደተኛ ታዳጊዎችን በኮክስ ባዛር እንከታተላለን፡፡ ጥናታችን ታዳጊዎችን፣ በተጨማሪም ይህ ጥናት ወንድምና እህቶቻቸውን፣ ወላጅና ተንከባካቢዎቻቸውን፣ መምህራንንና ሌሎች የማህበረሰብ አካላትን ያካትታል፡፡
ሀገራዊ ሁኔታ፡ የባንግላዲሽ ህዝብ እድገት እየቀነሰ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ከአምስቱ ባንግላዲሽ አንዱ ከ10 – 19 እድሜ አለው፡፡ ባንግላዲሽ በ2024 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ለመቀላቀል እየሰራች ቢሆንም ከአራቱ አንዱ ባንግላድ ከድህነት ወለል ይኖራል፡፡ ይህም ባንግላዲሽን ከአምስቱ ብዙ ህዝብ ካላቸው የአለማችን ደሀ ሀገሮች ዉስጥ አንዷ ያደርጋታል፡፡
ትምህርትና መማር፡ ባንግላዲሽ ባለፉት አስርት አመታት በሴቶች ትምህርት ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት አድርጋለች፡፡ ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር በመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተሳትፎ ሴቶች የተሻለ ተሳትፎ አላቸው፡፡ ይሁን እንጅ ወንዶቸ ከሴቶች በተሻለ መልኩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቅቃሉ፡፡ በቴክኒክና ሙያ እና በከፍተኛ ትምህርት የወንዶች ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ ነው፤ መረጃና ትክኖሎጂም ወንዶች የተሻለ ይጠቀማሉ፡፡ ድህነት ለሴቶችም ሆነ ለወንዶች ትምህርት ማቋረጥ ዋናው ምክንያት ነው፡፡ ይሁን እንጅ የሴቶች የትምህርት ተደራሽነት በማህበራዊ ልማዱ እየተየረ ነው፡፡ የቤት ዉስጥ ስራ ስለሚበዛባቸው የትምህርት የቤት ስራመስሪያ ጊዜ ስለሌላቸው አብዛኞቹ ሴቶች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ወደ ኋላ ይቀራሉ፡፡ ከትምህርት ሰዓት በኋላ የሚሰጠዉን ተጨማሪ ቱቶሪያልም ወላጆች ለወንድ ልጆቻቸው በማድላታቸው የተነሳ አይሳተፉም፡፡ ሌሎች ደግሞ በጋብቻ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ይፈናቀላሉ፡፡
አካላዊ ነፃነት፣ ምሉዕነትና ከጥቃት ነጻ መሆን፡ በቅርብ ጊዜያት የህጻናት ጋብቻን በመቀነስ ረገድ ጉልህ ለውጥ ቢኖርም፤ አሁንም ቢሆን ብዙ የባንግላዲሽ ልጃገረዶች በልጅነታቸው ያገባሉ፡፡ ሶስት አምስተኛ የሚሆኑት ልጃገረዶች የሚያገቡት በ18 አመታቸው ሲሆን አንድ ስምንተኛ የሚሆኑት ደግሞ በ15 አመታቸው ያገባሉ፡፡ ካገቡት ልጃገረዶች ዉስጥ ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት አካላዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል፤ አንድ አራተኛ የሚሆኑት ደግሞ በባሎቻቸው ፆታዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡ በተጨማሪም 90% የሚሆኑት ልጃገረዶች በማህበረሳቸው ዘንድ ፆታዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡
ጤና ፣ ስነ ምግብና ስነ ተዋልዶ ጤና፡ በህፃናት ጋብቻና በልጅነት ለመውለድ በሚደረግ ምርጫ ምክንያት፡ የታዳጊዎች እርግዝና በባንግላዲሽ የተለመደ ነው፡፡ ሶስት አምስተኛ የሚሆኑት ልጃገረዶች በ19 አመታቸው መውለድ ይጀምራሉ፡፡ እነዚህ ታዳጊ እናቶች ሳንሳዊ የሆነ የወሊድና የልጅ ክብካቤ አገልግሎት አያገኙም፡፡ የምግብ እጥረት በባንግላዲሽ ልጃገረዶች ዘንድ የተለመደ ነው፡፡ የ2014 ዲኤችኤስ (DHS) እንደሚያሳየው ከሆነ 31% የሚሆኑት ከ15 – 19 እድሜ ያላቸው ያገቡ ልጃገረዶች የምግብ እጥረት አለባቸው፡፡
የማህበራዊ ስነልቦና ደህንነት፡ በታዳጊዎች ማህበራዊ ስነልቦና ደህንነት ዙሪያ ያለው ማስረጃ በጣም ጥቂት ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት - በተለይ የከተማ ልጃገረዶች - በማህበረሰቡ በመገለላቸው፣ በፆታዊ ጥቃትና ህፃናት ጋብቻ አማካይነት ለአእምሮ ጤና ችግር ተጋላጭ ናቸው፡፡
ድምጽና ዉሳኔ ሰጭነት፡ በአሁኑ ሰዓት በስርዓተ ፆታ ላይ ያሉ አመለካከቶችና ልማዶች እየተለወጡ መጥተዋል፤ በተለይም በወጣት ሰዎች ዘንድ፡፡ ይሁን እንጅ የታዳጊዎች ድምጽና ዉሳኔ ሰጭነት ሴቶችን ለጋብቻና እናትነት ብቻ ያጠረው በወግ አጠባቂ ማህበራዊ ልማዶች አማካይነት የተወሰነ ነው፡፡ ይህም በማህበራዊ ተቋማትና ስርዓተ ፆታ (SIGI) የተገለጸ ነው፡፡ በዚህ ሪፖርት መሰረት ባንግላዲሽ ከሰባቱ የደቡብ እስያ ሀገሮች መካከል የመጨረሻውን ውጤት አስመዝግባለች፡፡ ወንድ ታዳጊዎች እየተሻሻለ የመጣ ነፃነት ሲኖራቸው ሴት ታዳጊዎች ግን ነፃነታቸው የተገደበ ነው፡፡ ይህም የሆነው ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን ከጾታዊ ትንኮሳና ጥቃት ለመጠበቅና የቤተሰቡን ክብር ለማስጠበቅ ነው፡፡
የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፡ ወደ 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ከ10 -14 እድሜ ላይ ያሉ ህጻናቶች ስራ ይሰራሉ፡፡ ከነዚህ ዉስጥ 31% የሚሆኑት ትምህርት እየተማሩ ስራ የሚሰሩ ናቸው፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስራ የሚሰሩ ሴት ህጻናቶች የሚገኙት በዋና ከተማዋ ዳካ ነው፡፡ ምንም እንኳ የተረጋገጠ ቁጥር ባይኖርም ቺታጎንግና ሲልሀት ተከታዩን ደረጃ ይይዛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ15 በታች እድሜ ያላቸው ሴት ታዳጊዎች በትምህርታዊ ስታቲስቲክስ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ ትልልቅ ታዳጊዎችም ቢሆኑ በጥቀሉ ያገቡ ሴቶች ጋር ተቀላቀለው ሪፖረት ተደርገዋል፡፡