ኔፓል
ኔፓል
የእኛ ምርምር በኔፓል ውስጥ በኑዋንቶት ፣ በጣና እና በሞራ ወረዳዎች በግምት 1,000 የሚሆኑ የጎልማሳ ሴቶችን እንከተላለን ፡፡
ሀገራዊ ሁኔታ፡ ኔፓል በቻይናና ህንድ መካከል የምትገኝ ትንሽዬ ተራራማ ሀገር ነች፡፡ ከአለማችን ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን በ2015 ካጋጠማት ርዕደ መሬት ለማገገም እየታገለች ያለች ሀገር ነች፡፡ አንድ አራተኛ የሚሆነው የኔፓል ህዘብ እድሜው ከ 10 – 19 ነው፡፡
ትምህርትና መማር፡ በመጀመሪያም ሆነ በሁለተኛ ደረጃ ትምሀርት የኔፓል ሴቶች ከወንዶች የተሻለ የመግባት እድል አላችው፡፡ ይሁን እንጅ ወንዶች ከሴቶች በተሻለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ያጠናቅቃሉ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተናንም ያልፋሉ፡፡ ይህም የሆነው በዎላጆች ምርጫና ለወንድ ልጆች በሚያደርጉት የበለጠ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ወንዶች ወደተሻሉ የግል ትመህርት ቤቶች ይላካሉ፤ የቤት ስራቸውን እንዲሰሩም የበለጠ ጊዜ ይሰጣቸዋል፡፡
አካላዊ ነፃነት፣ ምሉዕነትና ከጥቃት ነጻ መሆን፡ በቅርብ ጊዜያት የህፃናት ጋብቻ በፍጥነት እየቀነሰ ነው፡፡ ይሁን እንጅ 40% የሚሆኑጥ ከ20 - 24 አመት ያላቸው ወጣት ስቶች ያገቡት 18 አመት ሳይሆናቸው ነው፡፡ በታሪክ እነዚህ የህፃናት ጋብቻዎች የሚቀናበሩት በወላጆቻቸው ቢሆንም በአንዳንድ የኔፓል ክልሎች ግን በልጆች በራሳቸው የሚቀናበር የህፃናት ጋብቻ የተለመደ ሆኗል፡፡ ፆታዊ ትንኮሳና የስርዓተ ጾታ ጥቃት በጣም የተለመደ መሆኑን በጎልማሳ ሴቶች ላይ የተሰሩ ጥናቶች ያሳያሉ፤ይሁን እንጅ ስለ ታዳጊ ሴቶች የሚታወቅ ነገር የለም፡፡
ጤና ፣ ስነ ምግብና የስነ ተዋልዶ ጤና፡ በኔፓል በጾታና ሴቶች ዙሪያ ያለው አጉል ልማድ በጣም የጠነከረ ነው፡፡ ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከመድረሱ በፊት ስለጉርምስና ሊረዱ የሚችሉበት ጾታዊ ትምህርት ያላቸው ተደራሽነት በጣም ጥቂት ነው፡፡ ሴት ታዳጊዎች ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የተለያዩ ችግሮች ይገጥማቸዋል (ለምሳሌ - በአንዳንድ የኔፓል ክልሎች ልጃገረዶች በቻውፓዲ ይሰቃያሉ - ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ወቅት ቤታቸው ዉስጥ ተገንጥለው እንዲቀመጡ ይደረጋሉ) ፡፡ ሴት ታዳጊዎች ከጋብቻ በኋለም ቢሆን የወሊድ መቆጣጠሪያ የማግኘት እድላቸው ጠባብ ነው፡፡ ይህም የሆነው መውለድ እንደሚችሉ ለማረጋገጥ ሲባል ነው፡፡
የማህበራዊ ስነልቦና ደህንነት፡ ከወንዶች ጋር ሲነጻጸሩ የኔፓል ሴቶች ጥቂት የመንቀሳቀስና ማህበራዊ ግንኙነት አላቸው፡፡ ሴቶች ከወንዶች በላይ ብስጩና ድብርታም ናቸው፡፡ ይህም የሆነው የማህበራዊ ልማዱ በህይወታቸው ላይ እንዳያዝዙ ስለገደባቸው ነው፡፡
ድምጽና ዉሳኔ ሰጭነት፡ የኔፓል ወላጆች ለወንድ ልጅ ማድላታቸው የሴቶች ህይወት ከውልደታቸው ጀምሮ የተገደበ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ አብዛኞች ሀሳባቸውን ለመግለፅና በህይወታቸው ዙሪያ ዉሳኔ ለመስጠት ጥቂት እድል አላቸው፡፡ ያገቡ ሴቶች ድምጽ የሚታፈነው በባሎቻቸው ብቻ ሳይሆን በሴት አማቶቻቸውም ጭምር ነው፡፡
የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፡ ከልጅነት ጀምሮ ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ስራ ይሰራሉ፡፡ ከትንንሽ ታዳጊዎች ዉስጥ (እድሜያቸው ከ12–14 ከሆኑት), 18% የሚሆኑት ሴቶች በሳምንት ከ14 ሰዓት በላይ ይሰራሉ (ከ12% ወንዶች ጋር ሲነፃፀር)፡፡ 10% የሚሆኑት ሴቶች ደግሞ በሳምንት ከ28 ሰዓት በላይ ይሰራሉ (ከ3% ወንዶች ጋር ሲነፃፀር)፡፡ ከ15 – 17 እድሜ ካላቸው ታዳጊዎች ዉስጥ፣ 64% የሚሆኑት ሴቶች በሳምንት ከ43 ሰዓት በታች ሲሰሩ 3% የሚሆኑት ግን ከዚያ በታች ይሰራሉ (ከ58.5% እና 2% ወንዶች ጋር ሲነፃፀር)፡፡ ልጃገረዶችና ወጣት ሴቶች በገንዘብ ላይ ያላቸው ዉሳኔ ሰጭነት በጣም ዉስን ነው፤ ከብዙ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ተሳትፎም የተገለሉ ናቸው፡፡ ይህም ለወንዶችና ለጎልማሳ ሴቶች ያደላ እንደሆነ ያሳያል፡፡
ጥናታዊ ማስረጃዎች፡ የማስረጃ ንድፎቻችን እንደሚያሳዩት በኔፓል ሴት ታዳጊዎች ላይ የተሰሩ ማስረጃዎች ብዙ አቅሞች ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ ማስረጃዎች ደግሞ የሚያተኩሩት ትምህርት፣ የህፃናት ጋብቻ፣ አካላዊ ጤናና እነዚህን መቅረፅ የሚችለው የስርዓተ ፆታ ላይ ነው፡፡ ይሁን እንጅ አብዘኛው የሚታወቀው ስለ ታላላቅ ሴት ታዳጊዎች ወይም ስላገቡ ታላላቅ ሴት ታዳጊዎች ብቻ ነው፡፡