ጆርዳን
ጆርዳን
የእኛ ጥናት: - የተጋለጡ Jordanians እንዲሁም የፍልስጥኤም, አስተናጋጅ ማህበረሰቦች, ካምፖች እና መደበኛ tented የሰፈራ ውስጥ የሚኖሩ የሶሪያ እና የየመን ስደተኞች ጨምሮ በ ዮርዳኖስ, እስራኤል, ሳውዲ አረቢያ እና ሶሪያ ድንበር ትንሽ ወደብ አገር, እኛ ላይ 3,500 በጉርምስና የሚከተሉት ናቸው. የእኛ ምርምር የጎልማሳዎችን ራሳቸው ፣ ተንከባካቢዎቻቸው ፣ አስተማሪዎች እና ሌሎች የማህበረሰብ አባላትን ያጠቃልላል ፡፡
ሀገራዊ ሁኔታ፡ ካላት የህዝብ ቁጥር አኳያ ሲታይ ጆርዳን ብዙ የስደተኛ ቁጥር ያለባት ሀገር ነች፡፡ ከ1000 ህዝብ ዉስጥ 89ኙ ስደተኛ ነው፡፡ የዩኤንኤችሲአር (UNHCR) ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ በጁን 2018 ከ2 ሚሊዮን በላይ የፍልስጤም ስደተኞችና 660000 የሚሆኑ የሶሪያ ስደተኞች በጆርዳን ተመዝግበው ይገኛሉ፡፡ የመንግስት ምንጮች ግን የሶሪያ ህዝብ ግማሽ ያክሉ በጆርዳን ይገኛል ብለው ይዘግባሉ፡፡ ከነዚህ ዉስጥ 2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የፍልስጤም ስደተኞች ሲሆኑ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሶሪያዉያን ናቸው፡፡ አብዛኞች ስደተኞች ደሀ ናቸው፡፡ ለምሳሌ - 90% የሚሆኑት ጆርዳን ውስጥ የሚኖሩ የሶሪያ ስደተኞች ከድህነት በታች ይኖራሉ፡፡
ትምህርትና መማር፡ የጆርዳን ሴት ታዳጊዎች ከወንዶች በተሻለ በትምህርት ገበታ ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት ብዙ ወንዶች ስራ ለመስራት ሲሉ ትምህርት ስለሚያቋርጡና በመምህራቸው በሚደርስባቸው ጥቃት ተገፍተው ስለሚወጡ ነው፡፡ ከጆርዳንያውያን ዉስጥ 10% የሚሆኑት ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እድሜ የደረሱ ሴቶች ከትምህርት ውጭ ሲሆኑ የወንደች ቁጥር ደግሞ 15% ይሆናል፡፡ የሶሪያ ስደተኞች በትምህርት ገበታ ላይ የመገኘት ሁኔታ ድግሞ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ከ9 – 14 አመት እድሜ ያላቸው የሶሪያ ሴት ስደተኞች ውስጥ 72% የሚሆኑት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ከ15 – 17 አመት እድሜ ያላቸው የሶሪያ ሴት ስደተኞች ውስጥ ደግሞ 29% የሚሆኑት በትምህርት ገበታ ላይ ይገኛሉ፡፡ ለወንዶች ደግሞ ይህ ቁጥር 63% እና 22% በተካታታይነትይሆናል፡፡
አካላዊ ነፃነት፣ ምሉዕነትና ከጥቃት ነጻ መሆን፡ የጆርዳን ልጃገረዶች በተለይም የሶሪያ ስደተኞች የህፃናት ጋብቻ ጭግር በከፍተኛ ሁኔታ ተጋርጦባቸዋል፡፡ ከዘጠኙ አንዱ የሚሆኑት የጆርዳን ልጃገረዶች እና ከሶስቱ የሶሪያ ስደተኞች አንዷ ከ18 አመት በፊት ያገባሉ፡፡ በጆርዳን የሚኖሩ የሶሪያ ወንድ ታዳጊ ስደተኞች ደግሞ ለጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡ ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ጥቃቱ የሚደርስባቸው ባስጠጋቸው ማህበረሰብ ነው፡፡ በአንዳንድ ማህበረሰብ ዘንድ ልጆች የሚደርስባቸው ጥቃት የከፋ ከመሆኑ የተነሳ ወላጆች ለልጆቻቸ ደህንነት ሲሉ ከትምህርት ቤት ያስወጧቸዋል፡፡
ጤና ፣ ስነ ምግብና የስነ ተዋልዶ ጤና፡ የጆርዳን ታዳጊዎች ከስርዓተ ምግብ ጋር በተያያዘ የተለያዬ ችግሮች ይገጥማቸዋል፡፡ ጆርዳናዉያን ታዳጊዎች የክብደት መጨመር ይታይባቸዋል፡፡ የሶሪያ ስደተኞች ደገሞ በከፍተኛ ድህነት ምክንያት የምግብ ዕጥረት ያጋጥማቸዋል፡፡ የሶሪያ ስደተኞች በጋብቻ አማካይነት ለህፃናት እርግዝና የተጋለጡ ናቸው፡፡ ከአስሩ የሶሪያ እናቶች ዉልደት ውስጥ አንዱ ከ18 አመት በታች በሆኑ እናቶች የሚወለድ ነው፡፡በሌላ በኩል ደግሞ የጆርዳን ወንድ ታዳጊዎች ለሱስ ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸው ነው፡፡ ግማሽ የሚሆኑት በየቀኑ እንደሚያጨሱ አምነዋል፡፡ አንደንዛዥ ዕፅም አንገብጋቢ ጉዳይ እየሆነ ነው፡፡
የማህበራዊ ስነልቦና ደህንነት፡ አብዛኞቹ የጆርዳን ልጃገረዶች ስለወደፊቱ ህይወታቸው በጎ አመለካከት ያላቸው ሲሆን ከቤተሰቦቻቸውም ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላቸው አጠቃላይ አሰሳችን ይጠቁማል፡፡ ይሁን እንጅ ፤ ልጃገረዶች በድብርትና በምግብ እክል በሚጠቁ ጊዜ በአድሎና መድሎ አማካይነት እንክብካቤ አያገኙም፡፡ ምክንያም ወላጆች የልጆቻቸውን የወደፊት የጋብቻ ህወት አደጋ ላ መጣል አይፈልጉም፡፡ ምንም እንኳ የጆርዳን ወንድ ታዳጊዎች በህይወታቸው ‘ደስተኛ’ ቢሆኑም ብቸኝነት እንደሚያጠቃቸውና ችግራቸውን የሚያወሩት ሰው እንደሌላቸው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ ስደተኛ ታዳጊዎችም ድብርት ፣ ስጋት ፣ ጭንቀት እና እምሮን ከሚያዛባ ገጠመኝ (PTSD) ሪፖረት አድርገዋል፤ ሴቶች ስሜታቸውን ወደ ውስጥ ሲይዙት ወንዶች ግን ወደ ውጭ ያወጡታል፡፡
ድምጽና ዉሳኔ ሰጭነት፡ የጆርዳን ባህል የትውልድ ደረጃ ልዩነት ላይ ስለሚያተኩር የታዳጊዎች ዉሳኔ ሰጭነት በጣም የተገደበ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በተለይ ሴቶች ተጎጀዎች ናቸው፡፡ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀሩ የመንቀሳቀስ እድላቸው የተገደበ ነው፤ በተለይም ከጉርምስና በኋላ፡፡ የወላጆቻቸውን ዉሳኔም እነዲያከብሩ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሶሪያ ሴት ታዳጊ ስደተኞች በተለዬ መልኩ ተጎጀዎች ናቸው፡፡ በቀን ደረጃ ስናሰላው ከሶስቱ አንዷ ልጃገረድ ብቻ ከቤት የመውጣት እድል አላት፡፡
የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፡ ጆርዳን የወጣቶች ስራ አጥነት ቁጥር በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ዝቅተኛው የሴቶች ቅጥር ከሚታይባቸው የአለማችን ሀገሮች አንዷ ናት፡፡ ስደተኛ ወንድ ህፃናት ስራ ይሰራሉ፤ ለእነሱ የሚሰጠው ስራ ደግሞ በጣም በዝባዥና ክፍያቸውም በጣም ትንሽ ነው፡፡ ለሴት ታዳጊዎች ስራ ሙሉ በሙሉ የለም ማለት ይቻላል፡፡
ጥናታዊ ማስረጃዎች፡ የጆርዳን ታዳጊዎች ደህንነት ጉዳይ ልዩ አትኩሮትና እገዛ የሚፈልግ እንደሆነ የኛ ኩነታዊ ትንተና (አንድ ለሴትና አንድ ለወንድ) ይደመድማል፡፡ በወንድና ሴት ጆርዳናውያን ፣ በሶሪያ፣ እንዲሁም በፍልስጤም ስደተኞች መካከል ጉልህ ልዩነት ስላለ፡፡ የተለያዩ ወጣት ቡድኖችና ስደተኛ ማህበረሰቦች የሚያጋጥማቸው የእድሜ ፣ ስርዓተ ፆታና ዜግነት ተኮር ስጋቶችና መልካም አጋጣሚዎች ላይ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡